በቅርቡ አገልግሎት ለሚጀምረው የኤሌክትሮኒክ ፓስፖርት የሚያገለግል የዲጂታል ሰርተፊኬት ይፋዊ ቁልፍ የማመንጨት ሥነ ሥርአት ተካሄደ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

በቅርቡ አገልግሎት መስጠት ለሚጀምረው የኤሌክትሮኒክ ፓስፖርት የሚያገለግል የዲጂታል ሰርተፊኬት ይፋዊ ቁልፍ የማመንጨት ሥነ ሥርአት (Digital Certificate Key Ceremony) ተካሄደ፡፡ ሥነ ሥርአቱ የተከናወነው የብሔራዊ የሩት ሰርተፊኬት ባለስልጣን ሆኖ በሚያገለግለው የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ነው፡፡

የዲጂታል ሰርተፊኬት ይፋዊ ቁልፍ የማመንጨት ሥነ ሥርአቱን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገግሎት በቅንጅት ያከናወኑት ሲሆን፤ በመርሃ ግብሩ ላይም የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገግሎት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊትን ጨምሮ፤ ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች አቶ ጎሳ ደምሴ እና አቶ ቢቂላ መዝገቡ ተገኝተዋል፡፡

በሥነ ሥርአቱ ላይ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን ጨምሮ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገግሎት፣ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ግሩፕ፣ እና የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ፕሮግራም በታዛቢነት ተገኝተዋል፡፡

ለኤሌክትሮኒክ ፓስፖርት አገልግሎት የሚሆነው የዲጂታል ሰርተፊኬት ይፋዊ ቁልፍ የማመንጨት ሥነ ሥርአት የዓለም አቀፉን የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ስታንዳርድ (INTERNATIONAL CIVIL AVIATION ORGANIZATION - Doc 9303) ማዕከል ባደረገ መልኩ የተከናወነ ነው፡፡

በሥነ ስርአቱ ላይ የተገኙት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ እንደገለጹት የዲጂታል ሰርተፊኬት ዋና ጠቀሜታ በይነመረብን (Internet) በመጠቀም የሚካሄደው የኤሌክትሮኒክ ፓስፖርት አገልግሎት ለከፍተኛ የደህንነት ስጋት ተጋላጭ በመሆኑና በዓለማቀፍ ደረጃ ሕጋዊ ተቀባይነት እንዲኖረው የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡ ከዚህ አኳያ በዛሬው እለት የተካሄደው የዲጂታል ሰርተፊኬት ይፋዊ ቁልፍ የማመንጨት ሥነ ሥርአት በሀገራችን በቅርቡ የሚጀምረውን የኤሌክትሮኒክ ፓስፖርት አገልግሎት አጠቃላይ ደህንነት ከማረጋገጥ ባሻገር፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕጋዊ ተቀባይነትና ተዓማኒነት ያለው እንዲሆን ለማድረግ የሚያስችሉ አራት የኢንፎርሜሽን ደህንነት አገልግሎቶችን፤ ማለትም፡ ሚስጥራዊነትን (Confidentiality)፣ የመረጃን ሙሉዕነትና ትክክለኛነትን (Integrity)፣ የመረጃ ልውውጥ ተሳታፊዎችን ማነንነት ማረጋገጥ(Authentication) እና የመረጃ ልውውጥ መካካድን ማስቀረት (Non-repudiation) የሚያስችል እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሯ ጨምረዉ እንደገለጹት የፓስፖርት ማጨበርበርን እና የማንነት ስርቆትን ለመከላከል የኤሌክትሮኒክ ፓስፖርት ከፍተኛ ፋይዳ ያለዉ ሲሆን ይህም የፓስፖርት ባለቤቱን ማንነት በተሟላ መልኩ በማረጋገጥ ሊከሰት የሚችለውን የፎርጂድ አሰራርና የማንነት ስርቆት ሙሉ ለሙሉ የሚያስቀር እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር የኤሌክትሮኒክ ፓስፖርት አገልግሎት በየትኛውም ዓለም ሕጋዊ ተቀባይነት ያለው በመሆኑ በጉዞ ወቅትና በድንበር ላይ የሚኖሩ አሰራሮችን በእጅጉ የሚያቀላጥፍ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ብሔራዊ የሩት ሰርተፊኬት ባለስልጣን ሆኖ በማገልግለ ላይ ሲሆን፤ ለዚህ አገልግሎት የሚሆነውን “የይፋዊ ቁልፍ መሰረተ ልማት” የዳታ ማዕከል ነሃሴ 2016 ዓ.ም በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስመርቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች