ኢመደአና የስራና ክህሎት ሚኒስቴር በጋራ በሚሰሩባቸዉ ጉዳዮች ዙሪያ ዉይይት አደረጉ።

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር(ኢመደአ) እና የስራና ክህሎት ሚኒስቴር በጋራ በሚሰሩባቸዉ ጉዳዮች ዙሪያ ዉጤታማ ዉይይት አደረጉ።

ውይይታቸዉ የሥራ ስነ-ምህዳሩ ዘመኑን በዋጀ ቴክኖሎጂ በመደገፍ ምቹ፣ ፈጣን፣ ቀልጣፋና ፍትሃዊ ለማድረግ የሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነዉ፡፡ በቀጠይ ሁለቱ ተቋማት የትብብር ማዕቀፎችን በመለየት በዲጂታል ኢኮኖሚ ውስጥ ሰፊና ጥራት ያለው የሥራ ዕድል መፍጠር የሚያስችሉ ተግባራትን በቅንጅት ለማከናወን ተግባብተዋል፡፡

በዉይይቱ የተገኙት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ የተጀመሩ ሥራዎችን በማላቅ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትብብር መስራት ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል።

በመድረኩ የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ፣ የስራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል እንዲሁም የሁለቱም ተቋማት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

Publicador de Conteúdos e Mídias


የቅርብ ዜናዎች