የኢትዮጵያ አሁናዊ የሳይበር ዲፕሎማሲ ምን ይመስላል? በቀጣይስ ምን ይደረግ? በሚል ጥናታዊ ጽሁፍ ላይ ውይይት ተካሄደ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) በተቋም ደረጃ በየወሩ የሚያካሂደው “ኢንሳይት” የተሰኘ የውይይት መድረክ፤ የጥር ወር የውይይት መድረክ “የኢትዮጵያ አሁናዊ የሳይበር ዲፕሎማሲ ምን ይመስላል? በቀጣይስ ምን ይደረግ?” በሚል ርዕስ በቀረበ ጥናታዊ ጽሁፍ ላይ ተካሂዷል፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ እንደተናገሩት የሳይበር ደህንነት ዘርፍ ተለዋዋጭ፣ ኢ-ተገማች እና ፈጣን ለውጥ ያለበት በመሆኑ ሁሌም መማር እና የእውቀት ሽግግር ማድረግ በዘርፉ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመዝለቅና ተልዕኮን ለማሳካት ወሳኝ ሚናን ይጫወታል ብለዋል፡፡ ከዚህ አኳያ መድረኩ በዋናነት ኢመደአ በተሰማራበት የሳይበር ኢንዱስትሪ ላይ ያሉ አዝማሚያዎች እና ስትራቴጂክ አሰላለፎች ዙሪያ ለመማማርና ተደማሪ ሀገራዊ አቅም ለመገንባት የሚያስችል ነው።

የኢትዮጵያ አሁናዊ የሳይበር ዲፕሎማሲ ምን ላይ እንደሚገኝ፣ ተግዳሮቶቹ እና በቀጣይ ምን ማድረግ እንደሚገባ ያመላከተ ጥናታዊ ጽሁፍ በኢመደአ የሳይበር ዲፕሎማሲ ዲቪዥን ኃላፊ አቶ አብዱልባሲጥ አሕመድ የቀረበ ሲሆን፤ ጥናቱ የሀገራችንን ብሔራዊ ጥቅም በቀጣይነት ለማስከበር በሳይበር ዲፕሎማሲ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ ያመላከት ነው፡፡ የሳይበር ዲፕሎማሲ ጉዳይ የሀገራችን አንዱ የዲፕሎማሲ መስክ ሆኖ እንዲወጣ ተገቢውን ትኩረት መስጠት እንደሚገባ በጥናቱ ምክረ ሃሳብ ላይ ቀርቧል፡፡ በተለይም በሳይበር ዲፕሎማሲ ዙሪያ በሀገራችን ያለው የግንዛቤ ደረጃ ውስን ዝቅተኛ በመሆኑ በጉዳዩ ላይ ሰፊ የግንዛቤ ስራ መስራት እንደሚጠበቅ ተጠቁሟል፡፡

የውይይት መድረኩን የመሩት በውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት የአውሮፓና አሜሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል ዶ/ር ዳርእስከዳር ታዬ ጥናቱን መሰረት አድርገው ባነሱት ሃሳብ፤ የሳይበር ዲፕሎማሲ የቀጣዩ ወሳኝ የዲፕሎማሲ መስክ እና የሀገራትን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ አስቻይ ሚናን የሚጫወት ነው ብለዋል፡፡ በመሆኑም በመስኩ ላይ ትኩረት በማድረግ በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግ ጠቁመው፤ የሳይበር ዲፕሎማቶችን በማፍራት፣ በመስኩ ጥናትና ምርምሮችን በማድረግ፣ እንዲሁም መስኩን በተቀናጀ መልኩ ለመምራት የሚያስችሉ ተቋማዊ አቅሞችን በማዳበር በዓለማቀፍ መድረክ ላይ በጉልህ የሚታይ ተሳትፎን ማድረግ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

በውይይቱ መድረኩ ላይ በርካታ ሃሳቦች የተነሱ ሲሆን፤ በተለይም ኢትዮጵያ ከበርካታ ሀገራት ጋር በትብብር መስራትና በዓለም አቀፍ ግንኙነቶች ወሳኝ ሚና እንዲኖራት ብሎም በሌሎች አህጉር አቀፍና አለምአቀፍ ኩነቶች የመሪነት ሚናዋን በሳይበር ምህዳሩ ላይ ማሳየት እንድትችል በቅንጅትና በትብብር መስራት እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡

Agrégateur de contenus


የቅርብ ዜናዎች