በብሄራዊ የሳይበር ደህንነት ማዕቀፎች ላይ ለተለያዩ ክልሎች እና ከተማ መስተዳድሮች ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

በብሄራዊ የሳይበር ደህንነት ማዕቀፎች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የአተገባበር ሂደት ላይ ለተለያዩ ክልሎች እና ከተማ መስተዳድሮች ሲሰጥ የነበረው የመጀመሪያ ዙር ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡ በዚህ ስልጠና ላይ የቤንሻንጉል፣ የሐረሪ፣ የሶማሌ፣ የሲዳማ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት፣ እንዲሁም የድሬዳዋ ከተማ መስተዳደር ተሳታፊዎች ሆነዋል፡፡

ስልጠናውን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ከክልሎች እና ከተማ መስተዳድሮች የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮዎች ጋር በመተባበር ተሰጥቷል፡፡

የስልጠናው ዋና ዓላማ በኢመደአ የተዘጋጁ ሀገራዊ የሳይበር ደህንነትን ለማስጠበቅ በሚያስችሉ የሕግ ማዕቀፎች ዙሪያ ግንዛቤ መፍጠር እና የአተገባበር ሂደት ላይ ግልጽነትን መፍጠር ነው፡፡ በዚህም በኢመደአ በተዘጋጁ የተለያዩ የሳይበር ደህንነት ማዕቀፎች፤ የክሪቲካል ማስ ሳይበር ደህንነት መስፈርቶች ስታንዳርድ፣ የሳይበር ደህንነት ፖሊሲ፣ አዋጆች፣ መመሪያ እና ሀገራዊና አለማቀፍ የሳይበር ጥቃት አዝማሚያዎች ዙሪያ ግንዛቤ ለመፍጠር የሚያስችል ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

በስልጠናው ላይ ከክልሎች እና ከተማ መስተዳድሮች የተወጣጡ የፍትህና የፀጥታ አካለት፣ የመሬት አስተዳደር፣ የገቢዎች አስተዳደር እንዲሁም ከሌሎች ዋና ዋና ቢሮዎች የተወጣጡ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን በማድረግ ሂደት ውስጥ ለሳይበር ደህንነት ትኩረት መስጠት አስፈላጊ መሆኑን የስልጠናው ተሳታፊዎች ገልጸዋል፡፡ በዚህም የተቋማትን ብሎም የሀገሪቱን የሳይበር ደህንነት በማረጋገጥ ረገድ በኢመደአ የተዘጋጁ የተለያዩ የሳይበር ደህንነት ማዕቀፎች ፋይዳቸው ከፍተኛ በመሆኑ ሁሉም ክልሎች እና ከተማ መስተዳድሮች በአግባቡ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ሰልጣኞቹ ተናግረዋል፡፡

በስልጠናው ላይ ሀገራዊ የሳይበር ደህንነት ፖሊሲ እና አፈጻጸም ዙሪያ፤ እንዲሁም የቁልፍ መሰረተ ልማት ተቋማት እና የመንግስትና የግል ተቋማት የክሪቲካል ማስ ሳይበር ደህንነት መስፈርቶች ስታንዳርድን መተግበራቸው የሳይበር ጥቃትን ከመከላከል አኳያ በሚኖረው ፋይዳ ዙሪያ ሰፊ ግንዛቤ ለመፍጠር ተችሏል፡፡ ከዚህም ባሻገር በተለያዩ ክልሎች እና ከተማ መስተዳድሮች የሚገኙ ተቋማት ለሳይበር ደህንነት ማዕቀፎች ትግበራ የሰጡትን ትኩረትና ዝግጁነት ለመዳሰስና ቀጣይ የመፍትሄ አቅጣጫ በማስቀመጥ ረገድ የስልጠናው መሰጠት ፋይዳው ከፍተኛ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በመጀመሪያው ዙር ስልጠና ላይ ላልተሳተፉ ክልሎች እና ከተማ መስተዳድሮች በቀጣይ በሚዘጋጁ የስልጠና መርሃ ግብሮች ተደራሽ እንደሚደረግና ስልጠናው እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡

Sisältöjulkaisija


የቅርብ ዜናዎች