በዲጂታል ኢኮኖሚ ጉዞ የሳይበር ደህንነትና የዲጂታል መታወቂያ ሚና በሚል ርዕስ የፓናል ውይይት ተካሄደ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

በኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ጉዞ ላይ የሳይበር ደህንነት እና የዲጂታል መታወቂያ በሚኖራቸው ሚና ዙሪያ የፓናል ውይይት ተካሄደ፡፡ በፓናል ውይይቱ ላይ በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ዳይሬክተር አቶ ዮዳሄ አርአያሥላሴ፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ም/ዋና ዳይሬክተር ተወካይ አቶ ሃኒባል ለማ፣ እንዲሁም የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ዳይሬክተር አቶ አብዱላዚዝ ሻፊ በፓናሊስትነት ተሳትፈዋል፡፡

ለሀገራችን የዲጂታል ኢኮኖሚ ጉዞ ስኬት የዲጂታል መታወቂያ አስቻይ የሆነ ሚና እንደሚጫወት አቶ ዮዳሄ አርአያሥላሴ በፓናል ውይይቱ ወቅት ገልጸዋል፡፡ ዜጎች ማንነታቸውን እና ህጋዊ ሰውነታቸው የሚያረጋግጡበት ብሎም ወንጀልን ከሚከላከሉበት ቀዳሚው ጉዳይ ዲጂታል መታወቂያ እንደሆነ የገለጹት አቶ ዮዳሄ፤ ከዚህ አኳያ የዲጂታል መታወቂያ ለሀገራችን የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ የሚጫወተውን ሚና በአግባቡ በመረዳት ለስኬታማነቱ ተገቢውን ድጋፍ ማድረግ ከሁሉም ባለድርሻ አካላትና ከዜጎች ይጠበቃል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በፓናል ውይይቱ ላይ በፓናሊስትነት የቀረቡት አቶ ሃኒባል ለማ በበኩላቸው እንደገለጹት በዲጂታል 2025 ኢትዮጵያ ስትራቴጂ ላይ እንደተመላከተው ለሀገራችን የዲጂታል ኢኮኖሚ ጉዞ አስቻይ ከሆኑ ጉዳዮች መካከል የሳይበር ደህንነት እና የዲጂታል መታወቂያ ዋና ዋና ምሰሶዎች ናቸው ብለዋል፡፡ በመሆኑም የኢትዮጵያን የዲጂታል ኢኮኖሚ ግባታን ሂደት ለማሳካት የሳይበር ደህንነትና ሉዓላዊነት ማረጋገጥ ወሳኝ መሰረት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ ከዚህ አኳያ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የሀገራችንን የሳይበር ደህንነት በማረጋገጥ ለዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ጉዞ የራሱን ሚና በአግባቡ እየተጫወተ እንደሚገኝ አቶ ሃኒባል ለማ ገልጸዋል፡፡

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የተለያዩ የዲጂታል መሰረተ ልማት ዝርጋታዎችን እያከናወነ እንደሆነ የጠቀሱት በፓናል ውይይቱ ላይ የተሳተፉት አቶ አብዱላዚዝ ሻፊ፤ ከዚህ አኳያ “በዲጂታል ኢኮኖሚ ጉዞ የሳይበር ደህንነትና የዲጂታል መታወቂያ ሚና” በሚል ርዕስ በድሬዳዋ የተካሄደው የውይይት መድረክ የከተማዋን የዲጂታል ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ለማሳለጥ ከፍተኛ መነሳሳትን የሚፈጥር ነው ብለዋል፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የእምነት አባቶች፣ ከሁሉም የሀገሪቱ ክልሎች የመጡ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡ በእለቱ ከተካሄደው ውይይት ጎን ለጎንም የውይይት መድረኩን ታዳሚዎች የሚያሳትፍ የሳይበር ደህንነት ንቃተ ሕሊና ውድድሮችና በምናባዊ የቪዲዮ ጌም (Virtual Reality - VR) የታገዘ የሳይበር ደህንነት ንቃተ ሕሊና ማስጨበጫ ፕሮግራም ተካሂዷል፡፡

የቁልፍ መሰረተ-ልማት ደህንነት ለዲጂታል ሉዓላዊነት” በሚል መሪ ቃል ከጥቅምት 1/2017 ዓ.ም ጀምሮ እየተካሄደ የሚገኘው 5ኛዉ ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር ባለፉት ሶስት ሳምንታት ዉስጥ በተለያዩ ሁነቶች በአዲስ አበባ ከተማ ሲከበር የቆየ ሲሆን የወሩ የመጨረሻ መርሃ ግብሮች ጥቅምት 25 እና 26/2017 ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በተለያዩ የውይይት መድረኮች እየተካሄደ ይገኛል፡፡

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች