ለኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ጉዞ ስኬት የሳይበር ደህንነት እና የዲጂታል መታወቂያ ወሳኝ ሚናን እንደሚጫወቱ ተገለጸ

Applications imbriquées

Agrégateur de contenus

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጠንካራ የዲጂታል መረጃ ፍሰትን ለመፍጠር የሚያስችል ድረ-ገጽ አልምቶ አስረከበ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጠንካራ የዲጂታል መረጃ ፍሰትን ለመፍጠር የሚያስችል ድረ-ገጽ አልምቶ አስረከበ mer., 27 nov. 2024

የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ቸን ሃይ ጋር ተወያዩ

የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ቸን ሃይ ጋር ተወያዩ lun., 25 nov. 2024

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በሳይበር መከላከል ዙሪያ 30 የመከላከያ ሰራዊት አባላትን አሰልጥኖ አስመርቋል

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በሳይበር መከላከል ዙሪያ 30 የመከላከያ ሰራዊት አባላትን አሰልጥኖ አስመርቋል ven., 22 nov. 2024

“መከላከያ ኃይላችን ግዳጁን ከሚወጣባቸው ነባር ምህዳሮች ባሻገር አዲስ የጦርነት ምህዳር በሆነው የሳይበር ምህዳር ላይም አቅም ለመገንባት እየሠራ ነው” ክብርት ኢንጂነር አይሻ መሀመድ፣ የመከላከያ ሚንስትር

“መከላከያ ኃይላችን ግዳጁን ከሚወጣባቸው ነባር ምህዳሮች ባሻገር አዲስ የጦርነት ምህዳር በሆነው የሳይበር ምህዳር ላይም አቅም ለመገንባት እየሠራ ነው” ክብርት ኢንጂነር አይሻ መሀመድ፣ የመከላከያ ሚንስትር ven., 22 nov. 2024

Agrégateur de contenus

null ለኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ጉዞ ስኬት የሳይበር ደህንነት እና የዲጂታል መታወቂያ ወሳኝ ሚናን እንደሚጫወቱ ተገለጸ

የሳይበር ደህንነት እና የዲጂታል መታወቂያ የኢትዮጵያን የዲጂታል ኢኮኖሚ ጉዞ ለማሳካት እና የዲጂታል 2025 ስትራቴጂን እውን ለማድረግ አስቻይ ሚና እንደሚጫወቱ ተገለጸ፡፡

"የቁልፍ መሠረተ ልማት ደህንነት ለዲጂታል ሉዓላዊነት" በሚል መሪ ቃል ላለፉት ሦስት ሳምንታት ሲካሄድ የቆየው 5ኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር የማጠቃለያ መርሐ ግብር በድሬዳዋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ በመድረኩ ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር፤ የሳይበር ደህንነት እና የዲጂታል መታወቂያ ለዲጂታል ኢኮኖሚ ጉዞ ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።

የዲጂታል ኢኮኖሚን እየገነባች ለምትገኝ ሀገር የሳይበር ደህንነትን ማረጋገጥ የምርጫ ሳይሆን የሕልውና ጉዳይ ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሯ፤ ከዚህ አኳያ ለዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ከምንሰጠውን ትኩረት ባልተናነሰ ለሳይበር ደህንነትም መስጠት ይኖርብናል ብለዋል፡፡

የዲጂታል መታወቂያ የማንነትን መረጃን በመያዝ ወንጀልን ለመከላከል የሚኖረው ሚና የማይተካ በመሆኑ ለተግባራዊነቱ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ሲሉ ዋና ዳይሬክተሯ ገልጸዋል። በመሆኑም ስለ ዲጂታል መታወቂያ ለዜጎች ግንዛቤ በመስጠትና አገልግሎቶችን ከዲጂታል መታወቂያ ጋር ማስተሳሰር እንደሚገባ ጠቁመዋል።

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር በመድረኩ ላይ ባደረጉት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር፤ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 የሀገሪቱ ኢኮኖሚ በፈጠራና በክህሎት ላይ የተመሰረተ ኢንዲሆን ያስችላል ብለዋል።

መድረኩ የአስተሳሰብና የተግባር አንድነትን በመፍጠር በድሬዳዋ አስተዳደር ቀልጣፋ አገልግሎትን ተደራሽ በማድረግ ስማርት ከተማ ለመፍጠር የሚደረገውን ጉዞ እንደሚያግዝ ተናግረዋል።

ድሬዳዋ ከተማን ኢትዮጵያዊት የፍቅርና የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ ያስቀመጥነውን ራዕይ ከግብ በማድረስ በሀገሪቱ ምስራቃዊ ክፍል እና በቀጠናው አካባቢ ዋነኛ የንግድ፣ የአምራች ኢንዱስትሪና ቀልጣፋ የአገልግሎት ማዕከል ባለቤት ለማድረግ የዲጂታል መታወቂያ እና የሳይበር ደህንነት አስቻይ ሚና ይጫወታሉ ሲሉ አቶ ከድር ጁሀር ገልጸዋል፡፡