ለኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ጉዞ ስኬት የሳይበር ደህንነት እና የዲጂታል መታወቂያ ወሳኝ ሚናን እንደሚጫወቱ ተገለጸ

Aplicacions anidades

Publicador de continguts

"ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ሁሉን አቀፍ ለውጥ በሴቶች ተሳትፎ ይረጋገጣል’’ በሚል መሪ ቃል ዓለም አቀፉ የሴቶች ቀን በኢመደአ ተከበረ

"ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ሁሉን አቀፍ ለውጥ በሴቶች ተሳትፎ ይረጋገጣል’’ በሚል መሪ ቃል ዓለም አቀፉ የሴቶች ቀን በኢመደአ ተከበረ dv., 7 de març 2025

ለኢትስዊች አመራርና ሠራተኞች በሳይበር ደህንነት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ

ለኢትስዊች አመራርና ሠራተኞች በሳይበር ደህንነት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ dc., 5 de març 2025

በአድዋ ጦርነት የታየዉ ተምሳሌታዊ ተግባር የዲጂታል ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ ሊደገም እንደሚገባ የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሀሚድ ገለጹ

በአድዋ ጦርነት የታየዉ ተምሳሌታዊ ተግባር የዲጂታል ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ ሊደገም እንደሚገባ የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሀሚድ ገለጹ dl., 3 de març 2025

የሳይበር ደህንነትን የማስጠበቅ ሀገራዊ አቅም እያደገ መጥቷል፡፡

የሳይበር ደህንነትን የማስጠበቅ ሀገራዊ አቅም እያደገ መጥቷል፡፡ dl., 3 de març 2025

Publicador de continguts

null ለኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ጉዞ ስኬት የሳይበር ደህንነት እና የዲጂታል መታወቂያ ወሳኝ ሚናን እንደሚጫወቱ ተገለጸ

የሳይበር ደህንነት እና የዲጂታል መታወቂያ የኢትዮጵያን የዲጂታል ኢኮኖሚ ጉዞ ለማሳካት እና የዲጂታል 2025 ስትራቴጂን እውን ለማድረግ አስቻይ ሚና እንደሚጫወቱ ተገለጸ፡፡

"የቁልፍ መሠረተ ልማት ደህንነት ለዲጂታል ሉዓላዊነት" በሚል መሪ ቃል ላለፉት ሦስት ሳምንታት ሲካሄድ የቆየው 5ኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር የማጠቃለያ መርሐ ግብር በድሬዳዋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ በመድረኩ ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር፤ የሳይበር ደህንነት እና የዲጂታል መታወቂያ ለዲጂታል ኢኮኖሚ ጉዞ ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።

የዲጂታል ኢኮኖሚን እየገነባች ለምትገኝ ሀገር የሳይበር ደህንነትን ማረጋገጥ የምርጫ ሳይሆን የሕልውና ጉዳይ ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሯ፤ ከዚህ አኳያ ለዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ከምንሰጠውን ትኩረት ባልተናነሰ ለሳይበር ደህንነትም መስጠት ይኖርብናል ብለዋል፡፡

የዲጂታል መታወቂያ የማንነትን መረጃን በመያዝ ወንጀልን ለመከላከል የሚኖረው ሚና የማይተካ በመሆኑ ለተግባራዊነቱ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ሲሉ ዋና ዳይሬክተሯ ገልጸዋል። በመሆኑም ስለ ዲጂታል መታወቂያ ለዜጎች ግንዛቤ በመስጠትና አገልግሎቶችን ከዲጂታል መታወቂያ ጋር ማስተሳሰር እንደሚገባ ጠቁመዋል።

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር በመድረኩ ላይ ባደረጉት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር፤ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 የሀገሪቱ ኢኮኖሚ በፈጠራና በክህሎት ላይ የተመሰረተ ኢንዲሆን ያስችላል ብለዋል።

መድረኩ የአስተሳሰብና የተግባር አንድነትን በመፍጠር በድሬዳዋ አስተዳደር ቀልጣፋ አገልግሎትን ተደራሽ በማድረግ ስማርት ከተማ ለመፍጠር የሚደረገውን ጉዞ እንደሚያግዝ ተናግረዋል።

ድሬዳዋ ከተማን ኢትዮጵያዊት የፍቅርና የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ ያስቀመጥነውን ራዕይ ከግብ በማድረስ በሀገሪቱ ምስራቃዊ ክፍል እና በቀጠናው አካባቢ ዋነኛ የንግድ፣ የአምራች ኢንዱስትሪና ቀልጣፋ የአገልግሎት ማዕከል ባለቤት ለማድረግ የዲጂታል መታወቂያ እና የሳይበር ደህንነት አስቻይ ሚና ይጫወታሉ ሲሉ አቶ ከድር ጁሀር ገልጸዋል፡፡